ኢትዮጵያ “ዩጎስላቪያ” አይደለችም -አክሎግ ቢራራ (ዶር)
--ምርጫው ልማት ወይንም እልቂት ነው--- አክሎግ ቢራራ (ዶር) ጠ/ሚንስትር ዶር ዐብይ አህመድ ሥልጣን ከያዙበት ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ በፊት አይቶትና ሰምቶት የማያውቀውን የሰብአዊ መብት መከበር፤ በነጻ የመናገርና የመጻፍ፤ መንግሥትን የመተቸት፤ እንደልብ የመንቀሳቀስና የመደራጀት፤ የመሰብሰብ፤ ከአገር የመውጣትና የመግባት መብቶችን ተቀዳጅቷል። ችግሮችን በጋራና በሰላም የመፍታትና የኢትዮጵያን ጥልቀት ያለው የኋላ ቀርነትና የድህነት ሰቆቃ ለመቅረፍ እድሉ ከፍ ብሏል።